ከአፋር ህዝብ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
የአፋር ህዝብ ፓርቲ (አህፓ) ሀገራዊውን የፖለቲካ ምህዳር መስፋትን ተከትሎ ወደ ሀገር ከተመለሰ እነሆ ሁለት ዓመት አስቆጥሯል። ፓርቲያችን ወደ ሃገር ከገባበት ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ፖለቲካዊና ማህበራዊ መስኮች ሃገራዊ ግዴታውን እየተወጣ ይገኛል። የአፋር ህዝብ ፓርቲ በሃገራችን የተጀመረውን ረፎርም በአጭር ጊዜ ዉስጥ ያስመዘገባቸው የለውጥ ሂደቶችን ይደግፋል ያበረታታልም። ይሁንና በዚህ የለውጥ ሂደት ዉስጥ ወክለነዋል የምንለው የአፋር ህዝብ እንደ ህዝብ በሰላም የመኖር ዋስትና ፤ እንዲሁም እንደ ክልል ለመቀጠል የተደቀነበት ስጋት መቀረፍ አለመቻሉ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ለዚህ ስጋት ምንጭ የሆነው በአፋር አርብቶ አደሮችና በሶማሌ ክልል መካከል ለዘመናት መፍትሄ ያላገኘው ጦርነት በዋናናት ሊጠቀስ ይችላል። ይህ ለዘመናት ሲንከባለል የመጣውና በሶማሌ ክልላዊ መንግስት አዝማችነት እየተካሄደ ያለዉን የግዛት ማስፋፋት ጦርነት ከፌዴራል መንግስት እልባት አለማግኘቱ መላውን የአፋር ህዝብ ቁጭትና ቁጣ ዉስጥ አስገብቶታል።
ፓርቲያችን ይህን ጉዳይ አስመልክቶ የፌደራል መንግስት ህገ-መንግስቱን ማዕከል ያደርገ መፍትሄ መሰጠት አለበት በማለት ላለፉት ሃያ ዓመታት ለኢትዮጵያ መንግስትና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሲያስታዉቅ ቆይቷል። ይሁንና የፌዴራል መንግስት እልባት ሳያገኝለት ወይም ፍላጎት ሳይኖረው በመቅረቱ የንጹሃን ዜጎቻችን ህይወት በየቀኑ እየተቀጠፈ ይገኛናል። ፓርቲያችንም ለህግ የበልይነትና ለዘላቂ ሰላም ቅድሚያ በመስጠት በሶማሌ ልዩ ሃይልና ከባድ መሳሪያ በታጠቁ የተቀናጁ ሐይሎች ህዝባችን እንደቅጠል ሲረግፍና ሲታመስ እያየን መንግስት መፍትሄ ያመጣል በሚል ተስፋ እስካሁ ታግሰናል።
ተጨማሪ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ